መዝሙር 22:22-26

መዝሙር 22:22-26 NASV

ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ። እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤ እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት። እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው። በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ። ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!