መዝሙር 22:19-24

መዝሙር 22:19-24 NASV

አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት። ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ። ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ። እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤ እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት። እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።