መዝሙር 20:4-7

መዝሙር 20:4-7 NASV

የልብህን መሻት ይስጥህ፤ ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ። በአንተ ድል ደስ ይበለን፤ በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን። እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ። እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ። የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል። እነዚህ በሠረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤ እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።