እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል። ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤ እግሬም አልተንሸራተተም። ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም። እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤ ከእግሬም ሥር ወደቁ። አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤ ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ። ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤ እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም ረገጥኋቸው። በሕዝብ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የሕዝቦች መሪ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ። የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።
መዝሙር 18 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 18
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 18:34-45
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች