መዝሙር 144:12-15

መዝሙር 144:12-15 NASV

ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ። ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣ የተሞሉ ይሁኑ፤ በጎቻችን እስከ ሺሕ ይውለዱ፤ በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺሕ ይባዙ። ከብቶቻችን ይክበዱ፤ አይጨንግፉ፤ አይጥፉም። እኛም በምርኮ አንወሰድ፤ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ። ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።