መዝሙር 142:4-5

መዝሙር 142:4-5 NASV

ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤ ስለ እኔ የሚገድደው የለም፤ ማምለጫም የለኝም፤ ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።