ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል? ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል። እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም። እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል። ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም። እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ነፍስህንም ይንከባከባታል። እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።
መዝሙር 121 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 121
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 121:1-8
6 రోజులు
ጸሎት ስጦታ ነው፣ ድንቅ የሆነ ከሰማዩ አባታችን ጋር ህብረት የምናደርግበት እድል ነው። በዚህ የ6 ቀን እቅድ ውስጥ ኢየሱስ ስለጸሎት ያስተማረውን አብረን የምናስስ እና ቀጣይነት ያለው ጸሎት በትልቅ ድፍረት መጸለይ የምንችልበትን ሂደት እንዳስሳለን።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች