መዝሙር 119:41-48

መዝሙር 119:41-48 NASV

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ወደ እኔ ይምጣ፤ ማዳንህም እንደ ቃልህ ይላክልኝ። በቃልህ ታምኛለሁና፣ ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ። ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ። ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ። ሥርዐትህን እሻለሁና፣ እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ። ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም። እኔ እወድደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።