መዝሙር 118:18-22

መዝሙር 118:18-22 NASV

መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም። የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ጻድቃን በርሷ በኩል ይገባሉ። ሰምተህ መልሰህልኛልና፣ አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።