የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ። የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤ የሲኦልም ጣር አገኘኝ፤ ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ። እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ። እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤ አምላካችን መሓሪ ነው። እግዚአብሔር አላዋቂዎችን ይጠብቃል፤ እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ። ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና። አንተ ነፍሴን ከሞት፣ ዐይኔን ከእንባ፣ እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።
መዝሙር 116 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 116
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 116:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች