መዝሙር 109:21-26

መዝሙር 109:21-26 NASV

አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ። እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና። እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ። ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ። ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።