ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም። ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት። ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው። በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ።
መዝሙር 106 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 106
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 106:9-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች