መዝሙር 106:24-31

መዝሙር 106:24-31 NASV

ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም። በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጕረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም። በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤ ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ። ራሳቸውን ከበኣል ፌጎር ጋራ አቈራኙ፤ ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤ በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ መቅሠፍትም በላያቸው መጣ። ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፤ ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።