ምሳሌ 30:7-9

ምሳሌ 30:7-9 NASV

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ሁለት ነገር እለምንሃለሁ፤ እነዚህንም ከመሞቴ በፊት አትከልክለኝ፤ ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ። አለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።