የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ይህ ነው፤ ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፤ “እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ደነዝ ነኝ፤ ሰው ያለው ማስተዋል የለኝም። ጥበብን አልተማርሁም፤ ስለ ቅዱሱም ዕውቀት የለኝም። ወደ ሰማይ የወጣ፣ የወረደስ ማነው? ነፋስን በእጁ ሰብስቦ የያዘ ማነው? ውሆችንስ በመጐናጸፊያው የጠቀለለ ማነው? የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማነው? ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? የምታውቅ ከሆነ እስኪ ንገረኝ! “የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው። በርሱ ቃል ላይ አንዳች አትጨምር፤ አለዚያ ይዘልፍሃል፤ ሐሰተኛም ያደርግሃል። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሁለት ነገር እለምንሃለሁ፤ እነዚህንም ከመሞቴ በፊት አትከልክለኝ፤ ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ። አለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።
ምሳሌ 30 ያንብቡ
ያዳምጡ ምሳሌ 30
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ምሳሌ 30:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች