ምሳሌ 27:9-17

ምሳሌ 27:9-17 NASV

ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል። የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል። ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሠኘው፤ ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ። አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም። ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ ለባዕድ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ዐግተው። ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣ እንደ ርግማን ይቈጠራል። ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤ እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትን በእጅ እንደ መጨበጥ ነው። ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}