ምሳሌ 26:16-19

ምሳሌ 26:16-19 NASV

በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይልቅ፣ ሰነፍ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥራል። በሌሎች ጠብ ጥልቅ የሚል መንገደኛ፣ የውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው። ትንታግ ወይም የሚገድል ፍላጻ እንደሚወረውር እብድ፣ “ቀልዴን እኮ ነው” እያለ ባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።