ምሳሌ 23:1-8

ምሳሌ 23:1-8 NASV

ከገዥ ጋራ ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣ በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ ሆዳም ብትሆን እንኳ፣ በጕረሮህ ላይ ካራ አጋድምበት፤ የርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ ምግቡ አታላይ ነውና። ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ። በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፣ ወዲያው ይጠፋል፤ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበርራል። የሥሥታምን ምግብ አትብላ፤ ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤ ሁልጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤ “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ ልቡ ግን ከአንተ ጋራ አይደለም። የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።