የልብ ዕቅድ የሰው ነው፤ የአንደበት መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል። የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቷል፤ ክፉዎችንም እንኳ ለጥፋት ቀን አዘጋጅቷል። እግዚአብሔር በልብ የሚታበዩትን ሁሉ ይጸየፋል፤ እነርሱም ከቅጣት እንደማያመልጡ በርግጥ ዕወቅ። በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል። የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሠኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ ዐብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል። ከጽድቅ ጋራ ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል። ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ እግዚአብሔር ግን ርምጃውን ይወስንለታል።
ምሳሌ 16 ያንብቡ
ያዳምጡ ምሳሌ 16
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ምሳሌ 16:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች