ምሳሌ 13:13-16

ምሳሌ 13:13-16 NASV

ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል። የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል። መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤ የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ ሞኝ ግን ቂልነቱን ይገልጣል።