“በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሷል፤ አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል። እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ እንደ ጠጣችሁ፣ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፤ ይጠጣሉ፤ አብዝተውም ይጠጣሉ፤ ከዚህም በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ። ነገር ግን በጽዮን ተራራ ነጻ መውጣት ይሆናል፤ የያዕቆብ ቤትም እርሷ የተቀደሰች ትሆናለች፤ ርስታቸውን ይወርሳሉ። የያዕቆብ ቤት እሳት፣ የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ ከዔሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሯል።
አብድዩ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ አብድዩ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አብድዩ 1:15-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች