ዘኍልቍ 26:52-56

ዘኍልቍ 26:52-56 NASV

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ። በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል። የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል። እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።”