ዘኍልቍ 26:1-51

ዘኍልቍ 26:1-51 NASV

ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በሄኖኅ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤ በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤ በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤ በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤ እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት። ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤ የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም። የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ። የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤ በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤ በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤ በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤ በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤ በአሮዲ በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤ በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣ በፉዋ በኩል፣ የፉዋውያን ጐሣ፣ በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣ በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺሕ ሦስት መቶ ነበሩ። የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ የምናሴ ዘሮች፤ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤ የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣ በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣ በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣ በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣ በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣ በአፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣ የአፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ። እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ። የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣ በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤ የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ። የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣ በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣ በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣ በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጐሣ፣ በሑፋም በኩል፣ የሑፋማውያን ጐሣ፤ የቤላ ዘሮች በአርድና በናዕማን በኩል፤ በአርድ በኩል፣ የአርዳውያን ጐሣ፣ በናዕማን በኩል፣ የናዕማናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ። የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች። እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ስድሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በዪምና በኩል፣ የዪምናውያን ጐሣ፣ በየሱዊ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤ እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣ በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣ በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ። አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው። እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣ በዬጽር የዬጽራውያን ጐሣ፤ በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ። እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። በአጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።