ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ተሸበረ፤ በርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሀት ተውጦ ነበር። ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ ከወንዙ ዳር ባለች በትውልድ አገሩ በምትገኝ በፐቶር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤ “እነሆ፤ ከብዛቱ የተነሣ ምድሩን የሸፈነ ሕዝብ ከግብጽ ወጥቶ በአቅራቢያዬ ሰፍሯል። ስለዚህ ይህን ሕዝብ መቋቋም ስለማልችል መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባትም ድል አድርጌ ከአገሪቱ ላስወጣቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል፤ አንተ የምትባርከው ቡሩክ፣ የምትረግመውም ርጉም እንደሚሆን ዐውቃለሁና።”
ዘኍልቍ 22 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘኍልቍ 22
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘኍልቍ 22:3-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች