ዘኍልቍ 13:17-20

ዘኍልቍ 13:17-20 NASV

ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ኔጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ። ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ። የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ? ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልቦ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ በኵር ፍሬ ይዛችሁ ኑ።” ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።