“ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን እብሪተኞች ሆኑ። ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም፤ ‘አንድ ሰው ቢፈጽማቸው በሕይወት የሚኖርባቸውን’ ሥርዐቶችህን ተላለፉ። እንቢተኞች ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ መስማትም አልፈለጉም። ብዙ ዘመን ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህ አማካይነት በመንፈስህ አስጠነቀቅሃቸው። ነገር ግን አላደመጡህም፤ ከዚህም የተነሣ ጎረቤቶቻቸው ለሆኑ አሕዛብ አሳልፈህ ሰጠሃቸው። አንተ ግን ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና ከምሕረትህ ብዛት የተነሣ፣ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም። “አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ። በደረሰብን ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛ በደለኞች ነን፤ አንተ ግን ትክክለኛውን አደረግህ። ነገሥታታችን፣ መሪዎቻችን፣ ካህናታችንና አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ትእዛዞችህን ወይም የሰጠሃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም። በገዛ መንግሥታቸው፣ በሰጠሃቸው ታላቅ በጎነትህና በፊታቸውም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም ምድር እንኳ፣ አንተን አላገለገሉም፤ ከክፉ መንገዳቸውም አልተመለሱም። “እነሆ፤ ዛሬም ባሮች ነን፤ አባቶቻችን ፍሬዋንና በረከቷን እንዲበሉ በሰጠሃቸው ምድር ባሮች ነን። ከኀጢአታችን የተነሣ የተትረፈረፈው መከር ሲሳይ የሆነው በላያችን ላስቀመጥሃቸው ነገሥታት ነው፤ እነርሱም ደስ እንዳሰኛቸው በሰውነታችንና በቀንድ ከብቶቻችን ላይ ያዝዛሉ። እኛም በታላቅ ጭንቀት ውስጥ እንገኛለን።
ነህምያ 9 ያንብቡ
ያዳምጡ ነህምያ 9
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ነህምያ 9:29-37
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች