ነህምያ 12:44-47

ነህምያ 12:44-47 NASV

በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና። እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ። ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።