ነህምያ 12:27-30

ነህምያ 12:27-30 NASV

የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤትጌልገላ፣ ከጌባዕና ከዓዝሞት አካባቢ ነው። ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ።