በዚያ ጊዜ፣ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ። የሚበሉት ምንም ምግብ ስላልነበራቸው ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ከእኔ ጋራ ሦስት ቀን ስለ ቈዩና የሚበሉትም ስለሌላቸው ለእነዚህ ሰዎች ዐዝንላቸዋለሁ፤ እንዲህ እንደ ተራቡ ወደ ቤታቸው ብሰድዳቸው አንዳንዶቹ ከሩቅ የመጡ ስለ ሆኑ በመንገድ ላይ ዝለው ይወድቃሉ።” ደቀ መዛሙርቱም መልሰው፣ “በዚህ ምድረ በዳ እነዚህን ለመመገብ የሚያስችል እንጀራ ከወዴት ይገኛል?” አሉት። እርሱም፣ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ሰባት” አሉት። እርሱም፣ መሬት ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቡን አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራ ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቈርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ ዐደሉት። እንዲሁም ትንንሽ ዓሣዎች ነበሯቸው፤ እርሱም ዓሣዎቹን ባርኮ እንዲያድሏቸው አዘዘ። ሕዝቡም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ። በዚያም አራት ሺሕ ያህል ሰዎች ነበሩ፤ ካሰናበታቸውም በኋላ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ጀልባ ገብቶ ዳልማኑታ ወደ ተባለ ስፍራ ሄደ።
ማርቆስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ማርቆስ 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማርቆስ 8:1-10
4 ቀናት
አመለካከትዎን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል በማስተካከል 4ቱን ቀናት ያሳልፉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በድል ለመጓዝ የእግዚአብሔርን አመለካከት እንዴት እንደጠበቁ ከተለያዩ ታሪኮች ይማሩ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች