ማርቆስ 13:33-37

ማርቆስ 13:33-37 NASV

ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን ስለማታውቁ ተጠንቀቁ! ትጉ! ጸልዩም! ይህም ቤቱን ለባሮቹ ትቶ፣ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፣ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል። “እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፣ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ፤ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ‘ተግታችሁ ጠብቁ!’ ”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች