ሚክያስ 7:8-13

ሚክያስ 7:8-13 NASV

ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ! ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል። እርሱን ስለ በደልሁ፣ እስኪቆምልኝ እስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቍጣ እቀበላለሁ፤ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ እኔም ጽድቁን አያለሁ። ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች። ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት፣ ድንበራችሁንም የምታሰፉበት ቀን ይመጣል። በዚያ ቀን ሰዎች፣ ከአሦር እስከ ግብጽ ከተሞች፣ ከግብጽ እስከ ኤፍራጥስ፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ። ከሥራቸው የተነሣ፣ በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።