ሚክያስ 7:1-7

ሚክያስ 7:1-7 NASV

ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ፣ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም። የሚታመን ሰው ከምድር ጠፍቷል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፤ ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል። እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዥው እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጕቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ። ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤ የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሷል፤ የአምላክ የፍርድ ቀን መጥቷል፤ የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሷል። ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ። ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፣ ምራት በዐማቷ ላይ ትነሣለች፤ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና። እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤ የድነቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።