ሚክያስ 4:1-2

ሚክያስ 4:1-2 NASV

በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ፣ ከተራሮችም ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ። ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፣ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።