ማቴዎስ 9:35-38

ማቴዎስ 9:35-38 NASV

ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ እንዲሁም ደዌንና ሕመምን ሁሉ እየፈወሰ በከተሞቹና በመንደሮቹ ዞረ። ሕዝቡም እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ተመልካች የለሽ ሆነው ባየ ጊዜ ዐዘነላቸው። ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች