“ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤ ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና። “ዐይን የሰውነት መብራት ነው፤ ስለዚህ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ መላው ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዐይንህ ታማሚ ከሆነ ግን መላው ሰውነትህ በጨለማ የተሞላ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ድቅድቅ ይሆን? “ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይችልም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወድዳል፤ ወይም አንዱን አክብሮ ሌላውን ይንቃል። እግዚአብሔርንና ገንዘብን በአንድነት ማገልገል አይቻልም።
ማቴዎስ 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 6:19-24
7 ቀናት
ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ርዕሶች ላይ አስተምራል ፣ ስለ ዘላለማዊ በረከት ፣ ስለ ዝሙት ፣ ስለ ፀሎት እና ሌሎችሞ ብዙ ርዕሶች አስተሞራል። በዚህ ዘመን ላሉ ሰዎች ይህ ምን ማለት ነው? ምን ትርጉም አለው? ይህ አጭር ቪዲዮ የእያንዳንዱን ቀን የኢየሱስን ክርስቶስን ትምህርት በምሳሌ ይገልፃል::
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች