ማቴዎስ 4:1-7

ማቴዎስ 4:1-7 NASV

ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። አርባ ቀን እና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። ፈታኙም ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት። ቀጥሎም ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ በመውሰድ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል።’” ኢየሱስም፣ “እንደዚሁም በመጻሕፍት፣ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ተጽፏል” ብሎ መለሰለት።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች