ማቴዎስ 23:8-12

ማቴዎስ 23:8-12 NASV

“እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ አስተማሪያችሁ አንድ ብቻ ነው፤ እናንተ ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁና። በሰማይ ያለ አንድ አባት ስላላችሁ፣ በምድር ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ። መምህራችሁ አንዱ ክርስቶስ ስለ ሆነ፣ ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ። ከመካከላችሁ ከሁላችሁ የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፣ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ግን ይከበራል።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች