ማቴዎስ 22:41-45

ማቴዎስ 22:41-45 NASV

ፈሪሳውያን ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፣ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ “ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?” እነርሱም፣ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል? “ ‘ጌታ ጌታዬን፤ “ጠላቶችህን ከእግሮችህ በታች እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ።” ’ ስለዚህ ዳዊት፣ ‘ጌታዬ’ ብሎ ከጠራው፣ እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች