ማቴዎስ 18:23-27

ማቴዎስ 18:23-27 NASV

“ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ፣ በባሪያዎቹ እጅ የነበረውን ሒሳብ ለመተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። ሒሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺሕ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት። አገልጋዩም ያለበትን ዕዳ መክፈል ስላቃተው እርሱ ራሱ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ንብረቱ ሁሉ ተሸጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። “በዚህ ጊዜ ባሪያው እግሩ ላይ ወድቆ፣ ‘ታገሠኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው። ጌታውም ዐዘነለትና ባሪያውን ማረው፤ ዕዳውንም ትቶለት አሰናበተው።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች