ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አትፍራ፤ እመን ብቻ እንጂ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው። ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። ሰዎቹም መሞቷን ስላወቁ ሣቁበት። እርሱ ግን እጇን ይዞ፣ “ልጄ ሆይ፤ ተነሺ” አላት። የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሥታ ቆመች፤ ኢየሱስም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት አዘዛቸው። ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳያወሩ አዘዛቸው።
ሉቃስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 8:49-56
7 ቀናት
በኢየሱስ ፀጋ እንዴት ነው እየተለወጥኩ ያለሁት?
8 ቀናት
ኢየሱስ ስለራሱ ማን ብሎ ይላል?
12 ቀናት
ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ሰዎችን ሲፈውስ ኃይሉንና ርኅራኄውን ያሳየበትን መንገድ መርምር። አንድ አጭር ቪዲዮ ኢየሱስ በእያንዳንዱ ቀን የፈወሰውን ባለ 12 ክፍል እቅድ ጎላ አድርጎ ያሳያል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች