“መብራትን አብርቶ በጋን ውስጥ ወይም ከዐልጋ ሥር የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁንም ወደ ቤት የሚገቡ ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅ ወደ ብርሃን የማይወጣ፣ የተደበቀ ነገር የለምና። እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ፤ ላለው ሁሉ ይጨመርለታልና፤ ከሌለው ሁሉ ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።” ከዚህ በኋላ የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ እርሱ ወዳለበት መጡ፤ እነርሱም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ ሊቀርቡ አልቻሉም። በዚህ ጊዜ፣ “እናትህና ወንድሞችህ ሊያዩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል” የሚል ወሬ ደረሰው። እርሱም መልሶ፣ “እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው” አላቸው።
ሉቃስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 8:16-21
6 ቀናት
አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች