እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።” ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፤ እኔ ከአንተ ጋራ ወህኒ ለመውረድም፣ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” አለው። ኢየሱስም፣ “ጴጥሮስ ሆይ፤ እልሃለሁ፤ ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ፣ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። ከዚያም ኢየሱስ፣ “ያለ ኰረጆ፣ ያለ ከረጢትና ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ምንም አልጐደለብንም” አሉ። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን ኰረጆም፣ ከረጢትም ያለው ሰው ይያዝ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ይግዛ። እላችኋለሁና፤ ‘ከዐመፀኞች ጋራ ተቈጠረ’ ተብሎ የተጻፈው በእኔ መፈጸም አለበት፤ ስለ እኔ የተጻፈው ፍጻሜው በርግጥ ደርሷል።” ደቀ መዛሙርቱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆ፤ ሁለት ሰይፎች እዚህ አሉ” አሉት። እርሱም፣ “ይበቃል” አላቸው።
ሉቃስ 22 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 22
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 22:32-38
5 ቀናት
ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች