ሉቃስ 22:2-6

ሉቃስ 22:2-6 NASV

የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ እንዴት አድርገው ኢየሱስን እንደሚያስወግዱት መንገድ ይፈልጉ ነበር። ሰይጣንም ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በተባለው ገባበት፤ ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ተነጋገረ። እነርሱም በዚህ ደስ አላቸው፣ ገንዘብ ሊሰጡትም ተዋዋሉ። እርሱም በነገሩ ተስማማ፤ አሳልፎ ሊሰጣቸውም ሕዝብ የማይገኝበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ጀመር።