ሉቃስ 18:40-42

ሉቃስ 18:40-42 NASV

ኢየሱስም ቆም ብሎ ሰውየውን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ፤ ወደ እርሱም በቀረበ ጊዜ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ዐይነ ስውሩም፣ “ጌታ ሆይ፤ ዳግም እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው። ኢየሱስም፣ “እይ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።