የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። በርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ በእናቱም ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል። ከእስራኤልም ሰዎች ብዙዎቹን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳቸዋል፤ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ፣ ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኀይል በጌታ ፊት ይሄዳል።”
ሉቃስ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 1:11-17
8 ቀናት
ኢየሱስ ስለራሱ ማን ብሎ ይላል?
9 ቀናት
የመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሐፍ የእስራኤላዊት ሴት የሆነችውን የሐናን ታሪክ ይዘግባል። የሕይወቷ ሁኔታ ያስጎነበሳት እና ተስፋ አስቆራጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እሷን ምሳሌ የምትሆን ፈሪሃ አምላክ ያላት ሴት አድርጎ ይገልጻታል። ይህ የንባብ እቅድ የሐናን የህይወት ታሪክ ለራሳችን ህይወት እንደ ምሳሌ ይወስደዋል። ከእኛ ጋር ያንብቡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች