ይሁዳ 1:13-16

ይሁዳ 1:13-16 NASV

የነውራቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ የተቈጡ የባሕር ማዕበል፣ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የሚጠብቃቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው። ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነው ሔኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ሲል ተንብዮአል፤ “እነሆ፤ ጌታ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳኑ ጋራ ይመጣል፤ ይህም፣ በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችን ሁሉ በክፋት መንገድ በሠሩት የዐመፅ ሥራና በክፋት በርሱ ላይ ስለ ተናገሩት የስድብ ቃል ሁሉ አጥፊነታቸውን ይፋ ለማድረግ ነው።” እነዚህ ሰዎች የሚያጕረመርሙና ሌሎችን ሰዎች የሚከስሱ ናቸው፤ ክፉ ምኞቶቻቸውን ይከተላሉ፤ በራሳቸው ይታበያሉ፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉም ሌሎችን ይክባሉ።