ኢያሱ 4:21-24

ኢያሱ 4:21-24 NASV

እስራኤላውያንንም እንዲህ አላቸው፤ “ልጆቻችሁ ወደ ፊት፣ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው አባቶቻቸውን ቢጠይቁ፣ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤ እኛ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን እንዳደረቀው ሁሉ፣ እናንተም እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ በፊታችሁ አደረቀው። ይህን ያደረገውም፣ የእግዚአብሔር ክንድ ብርቱ መሆኑን የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁና እናንተም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለዘላለም እንድትፈሩ ነው።”