ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤ በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብጽኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣ ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣ ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣ ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣ ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣ ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣ ሐጻርሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ በኣላ፣ ዒዪም፣ ዔጼም፣ ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሖርማ፣ ጺቅላግ፣ ማድማና፣ ሳንሳና ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው። በምዕራቡ በኰረብታዎች ግርጌ ያሉት ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ኤሽታኦል፤ ጾርዓ፣ አሽና ዛኖዋ፣ ዓይንገኒም፣ ታጱዋ፣ ዓይናም፣ ያርሙት፣ ዓዶላም፣ ሦኮን፣ ዓዜቃ፣ ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው። ጽናን፣ ሐዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣ ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣ ለኪሶ፣ ቦጽቃት፣ ዔግሎን፣ ከቦን፣ ለሕማስ፣ ኪትሊሽ፣ ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው። ልብና፣ ዔቴር፣ ዓሻን ይፍታሕ፣ አሽና፣ ንጺብ፣ ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው። አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋራ፣ እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣ አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ። በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ ደና፣ ዳቤር የምትባለው ቂርያትስና ዓናብ፣ ኤሽትሞዓ፣ ዓኒም፣ ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣ ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያት አርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣ ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣ ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። ቂርያትይዓይሪም የተባለችው ቂርያትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣ ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋራ በኢየሩሳሌም ዐብረው ይኖራሉ።
ኢያሱ 15 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢያሱ 15
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢያሱ 15:20-63
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች