ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲህም አለ፤ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤ አንተም ጩኸቴን ሰማህ። ጥልቅ ወደ ሆነው፣ ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ በላዬ ዐለፉ። እኔም፣ ‘ከፊትህ ጠፋሁ፣ ነገር ግን እንደ ገና፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ፣ እመለከታለሁ’ አልሁ። ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ፤ ጥልቁም ከበበኝ፤ የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ። ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ። “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች። “ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ። እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ‘ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።’ ” እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፤ ዮናስንም በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።
ዮናስ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ዮናስ 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዮናስ 2:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች