“የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ። ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም። “ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው? እስራቱንስ ማን ፈታለት? ምድረ በዳውን መኖሪያው፣ የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት። በከተማ ውካታ ይሥቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። በየተራራው ይሰማራል፤ ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል። “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን? እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን? ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ? እህልህን እንዲሰበስብልህ፣ በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን? “ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም። ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤ እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች። እግር እንደሚሰብረው፤ የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም። የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤ እግዚአብሔር ጥበብ ነሥቷታልና፤ ማስተዋልንም አልሰጣትም።
ኢዮብ 39 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢዮብ 39
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢዮብ 39:1-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች